ዕጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥቆማ ለመቀበል የወጣ ማስታወቂያ Hibret June 26, 2024

ዕጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥቆማ ለመቀበል የወጣ ማስታወቂያ

ዕጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥቆማ ለመቀበል የወጣ ማስታወቂያ

የሕብረት ኢንሹራንስ አ.ማ ባላአክሲዮኖች ባካሄዱት 29ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ ቁጥር SIB/48/2019 መሠረት የቦርዱ አባላት አስመራጭ ኮሚቴ መመረጡ ይታወቃል፡፡
በዚሁ መሠረት ኮሚቴው ዕጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ጥቆማ ከሰኔ 17 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ መስከረም 12 ቀን 2017 ዓ.ም ብቻ ስለሚቀበል በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያዎች በተለይም ቁጥር SIB/48/2019 እና SIB/32/2019 ላይ የተዘረዘሩትንና በሚከተለው ሁኔታ የቀረቡትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ዕጩዎችን እንድትጠቁሙ ለመላው የኩባንያችን ባለአክሲዮኖች ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

  1. የሕብረት ኢንሹራንስ ባለአክሲዮን የሆነና የቦርዱ አባል ሆኖ ለመስራት ፈቃደኛ የሆነ፣
  2. ዕድሜው 30 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆነ፣
  3.  በንግድ ሥራ አመራር የሥራ ልምድ ያለው፣ በተለይም በኢንሹራንስ ሥራ ልምድ ያለው ቢሆን ተመራጭ ይሆናል፣
  4. በማንኛውም ኢንሹራንስ ኩባንያ ሰራተኛ ያልሆነ፣
  5. ሐቀኛ፣ ታማኝና መልካም ዝና ያለው፣ በተለይም በማጭበርበር፣ እምነት በማጉደል፣ ትክክለኛ ያልሆነ የሂሳብ መግለጫ በማቅረብና በመሳሰሉት ተከሶ በፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ውሳኔ ተሰጥቶበት የማያውቅ፣
  6. በሌላ የፋይናንስ ድርጅት ውስጥ የቦርድ አባል ወይም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ያልሆነ፣
  7. በራሱ ወይም በሚመራው ወይም ዳይሬክተር በሆነበት ድርጅት ላይ የመክሰር ክስ ያልቀረበበት ወይም የኪሳራ ውሰኔ ያልተሰጠበት፣
  8. በኪሳራ ምክንያት ንብረቱ የዕዳ ማቻቻያ ሆኖ ያልተወሰደበት፣
  9. የባንክ ብድር ባለመክፈሉ ምክንያት ንብረቱ በሃራጅ ያልተሸጠ፣ተከሶ ያልተፈረደበት ወይም እሱ የሚመራው ወይም ዳይሬክተር የሆነበት ድርጅት ከገንዘብ ተቋማት የተበደረውን ገንዘብ ባለመክፈሉ ብድሩ ጤናማ ወዳልሆነ የብድር ሁኔታ ያልገባበት (NPL ያልሆነበት)፣
  10.  ከሚመረጡት የቦርድ አባላት 75% የመጀመሪያ ዲግሪ ወይም ከዚያ በላይ ሊኖራቸው የሚገባ ሲሆን የተቀሩት 25% ቢያንስ የ2ተኛ ደረጃ ትምህርት ያጠናቀቁ መሆን አለባቸው፣
  11. በቂ ስንቅ/ገንዘብ ሳይኖረው ቼክ ሰጥቶ ሂሳቡ ያልተዘጋበት፣
  12.  ታክስ ባለመክፈሉ ተከሶ ጥፋተኛ ያልተባለ፣
  13.  የቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ አባል ያልሆነ እና
  14. የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያዎች ላይ የተገለጹ ሌሎች መመዘኛዎችን የሚያሟሉ፡፡

በመሆኑም ጥቆማውን "ዕጩ የቦርዱ አባላትን ለመጠቆም የተዘጋጀ ቅፅ" በሚል የተዘጋጀውን ፎርም በመሙላት፤

  • ቴዎድሮስ አደባባይ አካባቢ በሚገኘው የሕብረት ኢንሹራንስ አ.ማ (ኩባንያ) ዋና መስሪያ ቤት 10ኛ ፎቅ የዋና ሥራ አስኪያጅ ፀሐፊ ቢሮ በተዘጋጀው መዝገብ ላይ በአካል ቀርቦ በማስመዝገብ መሰጠት ወይም
  • በመልዕክት ሳጥን ቁጥር 1156 ለሕብረት ኢንሹራንስ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ ጽ/ቤት በማለት መላክ ወይም
  • በኢሜል አድራሻችን nominationc2024@unic-ethiopia.com መላክ ይቻላል፡፡

ማሳሰቢያ

  1. የጥቆማ ማቅረቢያውን ቅፅ
    – ከሕብረት ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ፀሐፊ ቢሮ ወይም በኩባንያው ቅርንጫፍ መ/ቤቶች ወይም ከኩባንያው ድረ ገፅ www.unic-ethiopia.com ማግኘት ይቻላል፡፡
  2. ከመስከረም 12 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት በኋላ የሚቀርቡም ሆነ ከዚህ በኋላ በፖስታ ወይም በኢሜይል የሚደርሱ ጥቆማዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
  3. የሕግ ሰውነት ያለው ባለአክሲዮን ጥቆማ ሲያደርግ በጥቆማ ማቅረቢያ ቅፁ ላይ የተገለፁትን ማሳሰቢያዎች ተግባራዊ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
  4.  በተባዕት ፆታ የተገለፀው በሙሉ ለአነስታይ ፆታም ያገለግላል፡፡
  5.  ከሚጠቆሙት ዕጩዎች መካከል 1/3ኛ የሚጠቆሙት ከኩባንያው ጠቅላላ የተፈረመ አክሲዮን ውስጥ ከ2% በታች በያዙ ባለአክሲዮኖች ነው፡፡ የተቀሩት 2/3ኛ ዕጩዎች ደግሞ በሁሉም ባለአክሲዮኖች የሚጠቆሙ ናቸው፡፡
  6. ለተጨማሪ ማብራሪያና አስተያየት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፀሐፊ ቢሮ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0114671874 መደወል ይቻላል፡፡

የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ ሕብረት ኢንሹራንስ አ.ማ

Write a comment
Your email address will not be published. Required fields are marked *